Education

ትምህርት ቢሮ

ደብረ ብርሃን, ሸዋ
image Tibebu Gesesu

የትምህርት መምሪያው ራዕይ

በከተማ አስተዳደሩ በስልጣኔ በልማት እና በዲሞክራሲ ባህሉ የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰ ህብረተሰብ ተፈጥሮ ማየት፡፡

የትምህርት መምሪያው ተልዕኮ

በከተማው ትምህርትና ሥልጠናን በስፋት፣ በጥራትና በፍትሀዊነት በማዳረስ፣ የሕብረተሰቡን አመራር ተሣትፎ ባረጋገጠ አደረጃጀት ተነሳሽነቱ የጐለበተ፣ በመብቱ የሚጠቀም፣ ግዴታውን የሚወጣ፣ ምርታማነቱ የዳበረ፣ ለአጠቃላይ ልማት መምጣት ምክንያት የሚሆን ሰብአዊ ሀብት ማፍራት ነው።

የትምህርት መምሪያው የአሠራር እሴቶች (Values)

  • • የባለቤትነት ስሜት
  • • ውጤታማነትና ብቃት
  • • ፍትሃዊነት
  • • ተጠያቂነት
  • • አሳታፊነት
  • • አገልጋይነት
  • • ብዝሃነት

የትምህርት መምሪያው መርሆዎች (Principles)

  1. ያልተማከለ የትምህርትና ሥልጠና ሥርዓትን መከተል፣
  2. ለሁሉም ዜጐች ጥራት ያለውና የሕይወት ዘመን ትምህርትና ሥልጠና ማቅረብ፣
  3. ፖሊሲውና ስትራቴጂዎች ግልጽና ለችግሮች ምላሽ የሚሰጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
  4. በየደረጃው የቁጥጥርና የተጠያቂነት ሥርዓት መዘርጋቱንና መተግበሩን ማረጋገጥ፣
  5. በየደረጃው ብቁና በቂ ተቋማትንና የሰው ኃይልን ማደራጀት፣
  6. የትምህርትና ሥልጠና ዘርፎች የሚደጋገፉበትንና የሚናበቡበትን ሥርዓት መዘርጋት፣
  7. የውጤት ተኮር ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓትን መከተል፣

የሰው ሀይል

  1. 1ኛ ደረጃ መ/ራን ወ 274 ሴ 653 ድ 927
  2. 2ኛ ደረጃ መ/ራን ወ 369 ሴ 185 ድ 554
  3. ኬጅ መ/ራን ወ 0 ሴ 79 ድ 79
  4. ር/መ/ራን ም/ር/መ/ራን ሱፐርቫይዘር 95
  5. የአስተዳደር ሰራተኛ 205