ራዕይ
ጤናማ፣ ምርታማና የበለጸገ ኀብረተሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡
ተልዕኮ
ጥራቱን የጠበቀ፤ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ፓኬጅ በመስጠት እና በመቆጣጠር የህዝቡን ጤና ደህንነት መጠበቅ ነው፡፡
ዓላማ
- የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ ማሻሻል
- • ወደ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን የሚደረገውን ሂደት ማፋጠን
- • ማህበረሰቡን ከድንገተኛ የጤና አደጋዎች መጠበቅ
- • ወረዳ ትራንስፎርሜሽን
- • የጤና ስርዓት ምላሽ ሰጪነት ማሻሻል
እሴቶችና እምነቶች (Core Values)
4.1. ለተገልጋይ ቅድሚያ መስጠት
- • የምንሰራዉ ህብረተሰቡን ለማገልገልና የጤና ፍላጎቱን ለማርካት ነዉ፤
- • ለራሳችን እንዲደረግልን የምንፈልገዉን አገልግሎት ሁሉ ለተገልጋዮቻችን እናደርጋለን
- • ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ለሁሉም ህብረተሰብ ማዳረስ፤
- • መሰረታዊ የጤና አገልግሎትን በማዳረስ የህብረተሰቡን ጤና ማበልፀግና በሽታን መከላከል፤
- • ደረጃዉንና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አግለግሎት መስጠት፤
- • ለሦስት ነገሮች ቅድሚያ እንሰጣለን፡ ደንበኛ፣ ደንበኛ፣ ደንበኛ
4.2. ቅንጅታዊ አሠራር /መተባበር
- • የጋራ ግቦቻችንን ለማሳካት በመደጋገፍና በመግባባት መንፈስ መስራት፤
- • ገንዘብን፣ ንብረትንና ጊዜን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፤
- • የሥራ ድግግሞሽን ማስወገድ፤
- • ባለሀብቶች በጤናዉ ዘርፍ የላቀ ተሳትፎ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ማበረታታት፤