ራዕይ
የከተማችንን ፀጥታ አስተማማኝና የተረጋጋ እንዲሆን በማድረግ ለልማትና ዲሞክራሲ ግንባታ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮ ማየት
ተልዕኮ
ወንጀልንና ግጭትን በብቃት መከላከል የሚስችል የፀጥታ መዋቅር በመፍጠር በህ/ሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚታገስ የፀጥታ አስተባባሪ ሀይል እንዲኖረው በማድረግ በፍትህ አስተዳደር ስርዓት ውስጥ የፀጥታ አካላቱ አስተማማኝ የመፈፀም ብቃት እንዲኖረው ማስቻል ፡፡
በመምሪው የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራቶች
- • የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ/ማረጋገጥ/
- • ፖሊስና ሚሊሻን በተገቢው ማስተባበር መምራት
- • የህዝባችን የሰላም ችግር የሆኑትን ጉዳዮች በመለየት መፍታት
- • ህዝባችንን የፀጥታው ባለቤት ማድረግ
- • ጠንካራ የመረጃ ስርኣት በመዘርጋት ወንጀሎች ሳይከሰቱ ማምከን
- • ግጭትን በማጥናት እርቅ በመፈፀም ወደ ሰላም መቀየር
- • ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ቅድመ መከላከል ማድረግ
- • በት/ቤቶች የሰላም ክበባትና ም/ቤቶችን በማዋቀር ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንዲኖር ማድረግ
- • የሀይማኖት ፎረምና ጉባኤን ወደ ስራ በማስገባት የሀይማኖት መቻቻልና አብሮ መኖርን ማጎልበት/ማዳበር/
- • የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ በዓላቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ በማድረግ የህዝባችንን ሰላም ማረጋገጥ
- • ሚኒ ካቢኒ ፀጥታ ም/ቤት አማካሪ ም/ቤቶች ወደ ስራ በማስገባት የሰላም ማስለጫ እንዲሆኑ ማድረግ
- • የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር የህዝብ ውይይት በማድረግ ችግሮችን መፍታት
- • የመከላከያ እና ሌሎች ምልመላዎችን በመመልመል ወደ ማሰልጠና መላክ